ትግራይ፡ ከግጭቱ ጋር ተያይዞ በፌስቡክ እየተዘዋወሩ ያሉ የተጭበረበሩ ምሥሎች - bbc news አማርኛ

ትግራይ፡ ከግጭቱ ጋር ተያይዞ በፌስቡክ እየተዘዋወሩ ያሉ የተጭበረበሩ ምሥሎች - bbc news አማርኛ

Play all audios:

Loading...

ትግራይ፡ ከግጭቱ ጋር ተያይዞ በፌስቡክ እየተዘዋወሩ ያሉ የተጭበረበሩ ምሥሎች ዳታን በመቆጠብ ጽሑፍ ብቻ ለማንበብ 20 ህዳር 2020 በትግራይ ክልል ካለው ሁኔታ ጋር ተያይዞ የሚወጡ መረጃዎች በምሥልና በቪዲዮዎች የታገዙ ናቸው። ሁሉም ታዲያ ትክክለኛ ናቸው ማለት አይደለም። የቢቢሲ የመረጃ አጣሪ ቡድን


በብዛት በማኅበራዊ የትስስር ገጾች የተጋሩ ሐሰተኛ መረጃዎችን እንደሁልጊዜው ሁሉ ነቅሶ አውጥቷቸዋል። * ከሬዲዮ ሞገድ አፈና እስከ ርዕሰ መስተዳድር፡ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ማናቸው? * የፖፕ ፍራንሲስ ኢንታግራም ገጽ ሞዴሏን 'ላይክ' ካደረገ በኋላ ምርመራ እየተደረገ ነው * በባሕር


ዳር ከተማ ላይ ዳግም የሮኬት ጥቃት ተፈጸመ * ዶ/ር ቴድሮስ ህወሓትን ደግፈዋል ተብለው የቀረበባቸውን ክስ አስተባበሉ 1. የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተሳሳተ ፎቶ ጠቅላይ ሚኒስትርዐቢይ አሕመድ በወታደራዊ ዩኒፎርም ይታያሉ። ስልክ እያወሩ ይመስላሉ። ጦር አውድማ ላይ ተገኝተው መመርያ እየሰጡም


ይመስላል። ይህን ምሥል በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ታዬ ደንደአ ስም የሚገኝ የፌስቡክ ገጽ ተጠቅሞታል። አቶ ታዬ ደንደአ የተጠቀሙት ይህ ምሥል የተጭበረበረ ነው። Skip ብዙ የተነበቡ and continue reading ብዙ የተነበቡ * በሲዳማ ክልል "መፈንቅለ መንግሥት


ለማካሄድ ጥረት" በማድረግ የተጠረጠሩት ባለሥልጣን ያለመከሰስ መብታቸው ተነሳ * ከ240 በላይ ሰዎችን አሳፍሮ ወደ ለንደን እየበረረ የነበረ የሕንድ አውሮፕላን ተከሰከሰ * በኢትዮጵያ የተገኘው የኤምፖክስ ቫይረስ ዝርያ "ከፍተኛ የሞት መጠን" እና "ሥርጭት"


ያለው መሆኑ ተገለጸ * የፓይለቶች እና ጠፈርተኞች ሕክምና ባለሙያው ኢትዮጵያዊ End of ብዙ የተነበቡ በሳቸው ገጽ ሦስት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፎቶዎች ይታያሉ። ይህ የአቶ ታዬ ገጽ ላይ ያለውን ፎቶዎቹን የያዘው መረጃ ከአንድ ሺ ሰዎች በላይ አጋርተውታል። ነገር ግን በሪቨርስ ኢሜጅ ፍለጋ ከፎቶዎቹ


አንዱ የተጭበረበረ እንደሆነ ደርሰንበታል። ይህም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልክ እያወሩ ጦርነቱን እየመሩ መስለው የሚታዩበት ፎቶ ነው። ፎቶው ከዚህ በፊት አገልግሎት ላይ የዋለ ነው። ይኸው ፎቶ ለመጀመርያ ጊዜ ስለ አሜሪካ ሰራዊት በሚያወሳ ዜና ላይ አገልግሎት ላይ ውሎ ያውቃል። ዋናውን የፎቶ ቅጂ እዚህ ጋ


ማየት ይቻላል። ፎቶዎቹን ያስተያይዋቸው። ይህ ፎቶ አንድ ወታደር ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድን እንዲመስል ተደርጎ የተቀነባበረ ነው። የቱባው (ኦሪጅናሉ) ፎቶ ምንጭ የት ነው በሚል ቢቢሲ ፍለጋ አድርጎ በጌቲ ኢሜጅ ቋት ውስጥ አግኝቶታል። ወደ ጌቲ ኢሜጅ የገባውም በኦክቶበር 2017 ነው። ፎቶው


የተወሰደበት ትክክለኛ አድራሻም ዩክሬን ውስጥ ነው። ስለ ጉዳዩ ይበልጥ የተሟላ መረጃ ለመስጠት አቶ ታዬ ደንደአ አረዶ ጋር ደውለን ነበር። ለምን የተጭበረበረ ምሥል እንደተጠቀሙ ለመጠየቅ። ሆኖም አልተሳካልንም። 2. ተመቶ የወደቀው አውሮፕላን ተንቀሳቃሽ ምሥል አንድ ተንቀሳቃሽ ምሥል በስፋት በማኅበራዊ


የትስስር ገጾች እየተጋራ ነው። ይህም የኢትዮጵያ የጦር አውሮፕላን ተመትቶ ከሰማይ ላይ ሲከሰከስ የሚያሳይ ነው። አውሮፕላኑ በትግራይ ክልል ጥቃት ሲያደርስ እንደተመታ ተደርጎ ነው የቀረበው። ይህ ተንቀሳቃሽ ምሥል ሐሰተኛ እንደሆነ ደርሰንበታል። የዚህ የተጭበረበረ ቪዲዮ ምንጭ የት ነው በሚል


ባደረግነው ፍተሻ አርማ ከሚባል የሚሊተሪ ቪዲዮ ጌም የተቀናበረ እንደሆነ አውቀናል። ሐሰተኛ ቪዲዮ ለመሆኑ ምልክቶችን ማየት ይቻላል። ለምሳሌ ከጀርባው የሚታየው ሰማያዊ ቀለም የተዘበራረቀ መሆኑ፣ እንዲሁም አውሮፕላኑ ከመከስከሱ በፊት የሚታየው ጭስ ስለ መጭበሩ ምልክት ይሰጣል። የዚህ ተንቀሳቃሽ ምሥል


ትክክለኛው መነሻ በጃፓንኛ ምሥሎችን የሚጭን አንዳንድ ጊዜም የእንግሊዝኛ ትርጉም የሚያስቀምጥ የዩትዩብ ቻናል እንደሆነ ደርሰንበታል። አሁን ወደ ኢትዮጵያ ተቀናጅቶ እየተጋራ ያለው ተንቀሳቃሽ ምሥል ከዚህ የጃፓን ዩትዩብ ቻናል የተወሰደ ሲሆን፤ በተወሰነ መልኩ ማሻሻያ ተደርጎበታል። ይኸውም የቪዲዮው


መግቢያና መጨረሻ ላይ በጃፓንኛ የተጻፉ ነገሮችን እንዲወጡ ተደርገዋል። አንዳንዶቹ ትክክለኛ ቪዲዮዎች በዚህ ምሥል ላይ እንደተጨማሪ ገብተዋል። ምሥሎቹ ትክክለኛ ናቸው። ነገር ግን ከኢትዮጵያ የተገኙ አይደሉም። ምንጫቸው በ2016 በዮርዳኖስ አየር ኃይል ኤፍ 16 ሲከሰከስ የሚያሳየው ትክክለኛ ምሥል


ነው። 3. ከኢትዮኤርትራ ጥቃት ጋር በተያያዘ አሁን በሰሜን ኢትዮጵያ ካለው ሁኔታ ጋር ምንም ተያያዥነት የሌላቸው ሌሎች በርከት ያሉ የተጭበረበሩ ምሥሎች ማኅበራዊ ሚዲያው ላይ እየተጋሩ ይገኛሉ። አንዳንዶቹ ከሌላው ዓለም ተወስደው የተቀናበሩ ናቸው፤ አንዳንዶቹ ምሥሎች ደግሞ ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት


የነበሩ ናቸው። ለምሳሌ አንድ የፌስቡክ ገጽ አለ። የማእከላዊው መንግሥት እየወሰደ ያለውን እርምጃ የሚደግፍ ነው። የሚጠቀመው ምሥል ግን ከኡስቤኪስታን የተወሰደ ነው። የወታደራዊ አውሮፕላን ሮኬቶችን ሲተኩስ የሚያሳዩ ምስሎችን ተጠቅሟል። ምስሎቹ በትግራይ እየሆነ ያለውን ሁኔታ የሚያሳዩ መስለው


ቀርበዋል። ይህም በብዙ ሺ ሰዎች ተጋርቷል። ሐሰት ነው። ምሥሎቹን በደንብ ላጤናቸው "Uz Air Force A. Pecchi" የሚል ጽሑፍ ማየት ይችላል። Uz ኡዝቤኪስታን በምሕጻር ቃል ሲወከል ነው። A.Pecchi የሚለው ደግሞ የፎቶ አንሺው ስም ነው። አንቶኒ ፔቺ ነው ሙሉ ስሙ። በዚህ


ዓመት ጃንዋሪ ይህ ፎቶ አንሺ እነዚህን ምሥሎች በራሱ የፌስቡክ ገጽ ላይ አጋርቷቸው ነበር። 4. ከባሕርዳርና ጎንደር ጥቃት ጋር በተያያዘ አንዳንድ ሰዎች ወደ ባሕርዳርና ጎንደር የተተኮሱ ሮኬቶች ያደረሱትን ጉዳት ለማሳየት ሐሰተኛ ምስሎችን ተጠቅመዋል። ሌሎች ደግሞ ወደ አስመራ የተተኮሱ ሮኬቶች


ያደረሱትን አደጋ ለማሳየት እነዚህን የተጭበረበሩ ምስሎት ተጠቅመዋል። ይህ ምሥል ግን ትክክለኛ ምንጩ በቻይና የተከሰተ ፍንዳታ ነው። የቻይና የወደብ ከተማ ቲያንጂን በ2015 በአንድ ኬሚካል ማከማቻ መጋዘን ላይ የደረሰ ፍንዳታን የሚያሳዩ ምስሎች ናቸው በጎንደር፣ በባሕር ዳርና በአስመራ የደረሱ ጉዳቶች


መስለው እየቀረቡ ያሉት። ቢቢሲ ይህንን ጉዳት በጊዜው ዘግቦት ነበር። አንደኛው ምሥልም በዚያን ጊዜ ከተዘገበው ምሥል ቁርጥ እንድ ዓይነት እንደሆነ ማየት ትችላላችሁ። 5. አስመራ ላይ የተተኮሰ ሚሳኤል ቪዲዮ አንድ የፌስቡክ ገጽ በአስመራ ላይ የተደረገውን የሚሳይል ጥቃት የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምሥል


ነው በሚል ቪዲዮ አጋርቷል። ይህ የፌስቡክ ገጽ ጥቃቱ ሲፈጸም የሚያሳይ ቪዲዮ ነው ያለኝ በሚል 2 ሰዓት ሙሉ በቀጥታ ጥቃቱን የቀረጸው ይመስል ለተከታዮቹ አጋርቷል። ከሺ ጊዜ በላይ የተጋራው ይህ ቪዲዮ ከኤርትራ የተገኘ አይደለም። ቪዲዮው የተወሰደው በዚህ ዓመት በጃንዋሪ ወር ኢራን በኢራቅ የሚገኘውን


የአሜሪካ የጦር ሰፈር በሚሳይል ስታጠቃ ከሚያሳይ ቪዲዮ ነው። ቢቢሲ በኢራቅ የተፈጸመውን ጥቃት በተመለከተ ዘገባ ሰርቶ ነበር። ጥቃቱ በኤርትራ እንደደረሰ አድርጎ ካጋራው የፌስቡክ ገጽ ጋር ምን ያህል አንድ እንደሆነ አይቶ መረዳት ይቻላል።