በእሥር ላይ የሚገኙት የምክር ቤት አባላት የችሎት ውሎ – DW – 29 ጥር 2017

በእሥር ላይ የሚገኙት የምክር ቤት አባላት የችሎት ውሎ – DW – 29 ጥር 2017


Dw is ON AIR - VIEW NOW

Please note: this is Beta feature.


Play all audios:

Loading...

ሰብዓዊ መብቶችአፍሪቃበእሥር ላይ የሚገኙት የምክር ቤት አባላት የችሎት ውሎሰለሞን ሙጬ29 ጥር 2017ሐሙስ፣ ጥር 29 2017 በእነ አቶ ዮሐንስ ቧያሌው የክስ መዝገብ ሥር የሽብር ወንጀል ክስ ከቀረበባቸው 51ድ ተከሳሾች መካከል ዛሬ ሐሙስ ፍርድ ቤት የቀረቡ 16 ተከሳሾች ዐቃቤ ሕግ ያቀረበባቸውን


ክስ አልፈጸምንም በማለት ተከራከሩ።


https://p.dw.com/p/4q8Piፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ አዲስ አበባፎቶ ከማኅደርምስል፦ APማስታወቂያየችሎት ውሎ To play this audio please enable JavaScript, and consider upgrading to a web browser that supports HTML5


audio


ከሳሽ የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ በዛሬው የችሎት ውሎ የክስ መዝገቡን አሻሽሎ አቅርቧል። ተፈፀመ በተባለው ወንጀል ሞተዋል የተባሉ ሰዎችን የስም ዝርዝር እና ደርሷል ያለውን የንብረት ውድመት ማስረጃ አያይዟል። የተከሳሾች የእምነት ክህደት ቃል የመስጠት ሂደት ከተጠናቀቀ በኋላ ተከሳሾቹ ክደው የተከራከሩ


በመሆኑ ማስረጃዎቼን ለችሎቱ ለማሰማት ቀጠሮ ይሰጠኝ ሲልም ጠይቋል። ችሎቱም የዐቃቤ ሕግን 21 ምስክሮች ለማድመጥ ሂደቱ ከመጋቢት 5-12 ቀን 2017 ዓ. ም እንዲቀጥል ቀጠሮ ሰጥቷል።


በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሕገ-መንግሥት እና የሽብር ወንጀል ጉዳዮች ችሎት ዛሬ ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም የተሰየመው የተከሳሾችን የዕምነት ክህደት ቃል ለማድመጥ ነበር። ዐቃቤ ሕግም በተከሳሾች ተፈጽሟል ባለው ወንጀል ላይ ፍርድ ቤት አሻሽለህ ቅረብ ሲል ያዘዘውን የክስ መዝገብ አሻሽሎ ቀርቧል።


ተከሰሾች ተሻሽሎ የቀረበውን ክስ በችሎቱ ለ 20 ደቂቃ ተመልክተውታል።ተሻሽሎ በቀረበው የክስ መዝገብ ላይ ከ 1,100 በላይ ሰዎች ሞተዋል የሚለው ከእነ ስም ዝርዝራቸው፣ የተጎዱ እና የአካል ጉዳት የደረሰባቸውም እንዲሁ፣ እና በዚህ የወንጀል ድርጊት በሚሊዮን የሚገመት ንብረት ወድሟል የሚለው ተካቶ


ቀርቧል ሲሉ ከተከሳሽ ጠበቆች መካከል አንደኛው ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸን ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል።


ችሎቱም ትከሳሾች የቀረበባቸውን ክስ ስለመፈፀም አለመፈፀማቸው የእምነት ክህደት ቃል እንዲሰጡ አድርጓል። በችሎቱ የሁሉም ተከሳሾች ቃል በመቅረጸ ድምፅ የተቀዳ ሲሆን በመጀመርያ የእምነት ክህደት ቃላቸውን የሰጡት የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ዮሃንስ ቧያሌው ናቸው።  እሳቸው «የሽብር


ቡድን አመራር በመሆን፣ አባል በመሆን፣ በማደራጀት፣ ስትራቴጂ ሰነድ በማዘጋጀት እና ጽንፈኛ የሆነውን ፋኖን በመምራት የሽብር ወንጀል ፈጽሟል» የሚሉት ክሶች «በፈጠራ የተሞሉ ናቸው»፣ «መረጃ አልባና ከእውነት የራቀም ነው» ብለው ቃላቸውን ሰጥተዋል። 


ሁለተኛ የእምነት ክህደት ቃላቸውን የሰጡት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ክርስትያን ታደለ ናቸው። እሳቸውም «በዚህ ችሎት የቀረብኩት እና ለ550 ቀናት በግፍ እና በጭካኔ እገታ ውስጥ የምገኘው ለአንድ ደቂቃ እንኳን በጥፋተኝነት የሚያስቀጣ የሕግ መተላለፍ ስለፈፀምኩ ሳይሆን የአማራ


ሕዝብ የሚያነሳቸውን የሕልውና ጥያቄዎች በይፋ በማቅረቤ፣ በሕዝብ ላይ የሚፈፀምን ግፍና በደል በማስረጃ በመሞገቴ ነው» ሲሉ የቀረበባቸውን ክስ እንዳልፈፀሙ ተናግረዋል።


ችሎት የቀረቡት 16 ቱም ተከሳሾች በዐቃቤ ሕግ የተመሰረተብን ክስ የሀሰት ነው፣ ወንጀሉንም አልፈፀምንም ብለው መከራከራቸውንና ቀጥሎም ዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን ይዞ ቀርቦ ለችሎቱ ለማሰማት ቀጠሮ በመጠየቁ ሂደቱ ከ አንድ ወር ከስድስት ቀን በኋላ እንዲቀጥል ቀጠሮ መሰጠቱን ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ ለዶቼ ቬለ


ተናግረዋል።


ሰሎሞን ሙጬ


ሸዋዬ ለገሠ


ነጋሽ መሐመድ


መጋቤ ምላሽዎን ይላኩልንየርስዎ መጋቤ ምልሽማስታወቂያ