በዘንድሮው የዓለም ኢኮኖሚ መድረክ ስለ አፍሪቃ ምንምን ጉዳዮች ተነሱ?
Dw is ON AIR - VIEW NOW
Please note: this is Beta feature.
Play all audios:
የ2024 የዓለም የምጣኔ ሀብት መድረክ To play this audio please enable JavaScript, and consider upgrading to a web browser that supports HTML5 audio «ታማኝነትን መልሶ መገንባት»በሚል መሪቃል ከጎርጎሪያኑ ጥር 15 ጀምሮ ለ5
ተከታታይ ቀናት የተካሄደው ዓለም አቀፉ የምጣኔ ሀብት መድረክ በዛሬው ዕለት ፍፃሜውን አግኝቷል። በስዊዘርላንድ ዳቮስ በተካሄደው በዚህ መድረክ የጋዛ እና የዩክሬን አስከፊ ጦርነቶች ፣የሰው ሰራሽ አስተውሎት እመርታዎች እና የፈጠረው ስጋት እንዲሁም የኮቪድ 19 የጤና እክል ጥሎት ያለፈው የኢኮኖሚ
ድቀት እና ከፍተኛ የእዳ ቀውስ በመድረኩ ከተነሱ ጉዳዮች መካከል ናቸው። መንግሥታትና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች፣ ቢሊየነሮች፣ ሥራ ፈጣሪዎች፣ ባለሙያዎች እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተወካዮች በተገኙበት በዚህ መድረክ የጋናው ፕሬዝዳንት ናና አኩፎ-አዶ እና የሩዋንዳው ፖል ካጋሜ ከአፍሪካ
ቁልፍ ሰዎች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው።በመድረኩ የተገኘው DW ዘጋቢ አሹቶሽ ፓንዲ እንደሚለው በዚህ መድረክ የአፍሪቃ ተወካዮች የብድር እና የእዳ ቀውስን አጽንኦት ሰጥተው አንስተዋል። «በአፍሪካ ልዑካን እዚህ ለውይይት ከተነሱ አንዳንድ ዋና ዋና ነጥቦች መካከል በአስቸጋሪው የዕዳ ቀውስ እና
ከአበዳሪዎች ከሚመጡ ማንኛውም የእፎይታ መዘግየት ላይ ብዙ ትኩረት አለ። ያ ትልቅ ጉዳይ ነው።»የዳቮሱ የዓለም የኤኮኖሚ መድረክ ዛሬ በይፍ ተጀመረ ከዚህ በተጨማሪ የሃይል እጥረት ፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በኢኮኖሚ በማደግ ላይ ያሉ ብዙዎቹ የአፍሪቃ ሀገራት ከፍተኛ የብድር
ጫና ውስጥ መሆናቸው በመድረኩ የተነሱ ጉዳዮች ናቸው። መድረኩን የተከታተለው ጋዜጠኛ ፓንዲ እንደሚለው በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ዘንድም የአፍሪቃ ሀገራት የዕዳ ቀውስ ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ ነው። «የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት በእርግጥ ዝቅተኛ ኢኮኖሚ ካላቸው ከግማሽ በላይ የሚሆኑት
በከፍተኛ ጭንቀት እና ስጋት ውስጥ እንዳሉ ገልጿል። ኢትዮጵያ ያለፈው ታህሳስ እዳ መክፈል ከማይችሉ የአፍሪቃ ሀገሮች ውስጥ ሆናለች።እናም አሁን፣ ሀገራቱ ምን ያህል ገንዘብ እንዳላቸው እና ምን ያህል ማውጣት እንደሚችሉ በመሳሰሉ የገንዘብ ጉዳዮች ላይ ይህ ስጋት አለ። ለእነሱ የብድር ወጭም እየጨመረ
ነው።ስለዚህ ይህ አንዱ ጉዳይ ነው።» ከ60 በላይ የሀገር መሪዎችን ጨምሮ ከ2,800 በላይ ተሳታፊዎች በታደሙበት በዚህ መድረክ ከፖለቲካ መሪዎች መካከል የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ፣የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ፎን ደር ሌየን እና የቻይና ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ
ይገኙበታል። በጋዛ ጦርነት ቁልፍ ባለድርሻ አካላት፣ የእስራኤሉ ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ እና የኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር መሀመድ ቢን አብዱራህማን አልታኒ ግጭቱን ማስቆም በሚቻልበት መንገድ ላይ ተወያይተዋል። ዩአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከንም ከሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ጋር
በዝግ መክረዋል።ብሊንከን ከውይይቱ በኋላ ባደረጉት ንግግር አሜሪካ በሩዋንዳ እና በኮንጎ መካከል ያለውን ልዩነት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኗን ጠቅሰዋልትኩረት በአፍሪቃ፣አፍሪቃ በዳቮስ፣የኮንጎ ጦርነት። በቀጠሉት ሌሎች የአፍሪቃ ውይይቶችም የአህጉሪቱን ከፍተኛ
ቁጥር ያለው ወጣት ተደራሽ የሚያደርግ የስራ እድል ስለመፍጠር እና የስነ ሕዝብ አወቃቀር ጉዳዮች ተነስተዋል። የዓለም ኤኮኖሚ መድረክ ጉባዔ ከዚህ በተጨማሪ በተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም/UNDP/ እና በአፍሪካ መሪዎች ትብብር የተመሰረተው የቲምቡክቶ የሀብት ማሰባሰቢያ መርሀ-ግብርም አንዱ
የአፍሪቃ ጉዳይ ነበር።የአፍሪቃን የስራ ፈጠራ እና ጀማሪ የቴክኖሎጅ ኩባንያዎችን ለመደገፍ የተቋቋመው ይህ መርሀ ግብር የዶቼ ቬለው ፓንዲ እንደሚገልፀው በአፍሪቃ ቢቢሊዮን በሚቆጠር ዶላር መዋዕለ ንዋይ የማፍሰስ ዕቅድ አለው። «ዓላማው በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ውስጥ አንድ ቢሊዮን ዶላር የመዋዕለ
ንዋይ ለማፍሰስ ነው፣ ገንዘቡ መሰረት ያደረገው ኪጋሊ ላይ ነው። ለዚህ ነው ፕሬዝዳንት ካጋሚ የሀብት ማሰባሰቡን ለመጀመር የሶስት ሚሊዮን ዶላር እንደሚያዋጡ ያሳወቁት። ነገር ግን ገንዘቡ በተለያዩ ሀገራት ይሰራጫል ።» ያም ሆኖ የዳቮሱ ዓለም አቀፍ የምጣኔ ሀብት መድረክ በበርካታ ጉዳዮች ላይ ቃል
ቢገባም፤ በዝግጅቱ ወቅት የተሰጡ ሃሳቦች፣ ንግግሮች፣ ውይይቶች እና የተስፋ ቃሎች በመንግሥታት ላይ አስገዳጅ አንድምታ ስለሌላቸው ተፈፀሚነቱ ላይ ትችት የሚያነሱ በርካቶች ናቸው። በሌላ በኩል ለዚህ መድረክ አባልነት በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ዶላር ለስልታዊ የሽርክና ክፍያ ያስፈልጋል።በዳቮስ ጉባኤ ላይ
ለመገኘትም ተጨማሪ ወጪዎችን ይጠይቃል። ተቺዎች በጉባኤው ወቅት የሆቴሎች እና የምግብ ዋጋ ውድነትንም አጉልተው ያሳያሉ። ፀሀይ ጫኔ ታምራት ዲንሳ